Loading
አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x) ጌታን ፡ የሚያስቀድም ፡ በኑሮው ፡ በቤቱ አቅፎ ፡ እንደ ፡ ደገፈው ፡ እንደ ፡ እናት ፡ አባቱ ያ ፡ ነው ፡ የአምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ክብሩን ፡ የማይፈልግ በክፉ ፡ በደጉ ፡ ከቶ ፡ ማይበረግግ አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x) በትዕግሥት ፡ ጠብቁ ፡ አምላክ ፡ ይቅደም ፡ የሚል እራሱን ፡ በውርደት ፡ ከመስቀሉ ፡ ሚጥል ያ ፡ ነው ፡ ያምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ምኞቱን ፡ ያሟላ ለያዘው ፡ ቁም ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ የማይላላ አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x) ጌታ ፡ እንድቀድምልህ ፡ በኑሮው ፡ መከራ በእምባው ፡ እየታጀበ ፡ ለመዝሙር ፡ ሲጠራ ያ ፡ ነው ፡ የአምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ክብሩን ፡ የሰቀለ ያጋንንትን ፡ ሥልጣን ፡ በእምባው ፡ ያቃጠለ አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.