Loading
አንበጣ ፡ አይደለሁም ፡ ትንሽ ፡ ምናምንቴ ፈቃድን ፡ አልሰጠውም ፡ እንዲስቅ ፡ ጠላቴ በዘመኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ መልካሙን ፡ እናገራለሁ የኢየሱስ ፡ ወንጌል ፡ በህይወቴ ፡ ላይ ፡ ሲሰራ ፡ አያለሁ አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x) አትደግ ፡ ብሎ ፡ ትላንት ፡ የረገመኝ ጉድ ፡ ትሆናለህ ፡ ታያለህ ፡ እኮ ፡ ያለኝ የርግማን ፡ ትንቢቱ ፡ ይፍረስ ፡ በጌታ ፡ ሥም ልቤማ ፡ ደንግጦ ፡ ለርሱ ፡ እጅ ፡ አልሰጥም አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x) ከዘር ፡ ማንዘሮቼ ፡ ተወራርሶ ፡ የመጣ ነፃነት ፡ ከልክሎ ፡ መንገዴን ፡ የዘጋ ዛሬ ፡ በየሱስ ፡ ስም ፡ ጉልበቱ ፡ ይመታ ወዳጄ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ በቤቴ ፡ ላይ ፡ ጌታ አንበጣ ፡ አይደለሁም ፡ ትንሽ ፡ ምናምንቴ ፈቃድን ፡ አልሰጠውም ፡ እንዲስቅ ፡ ጠላቴ በዘመኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ መልካሙን ፡ እናገራለሁ የኢየሱስ ፡ ወንጌል ፡ በህይወቴ ፡ ላይ ፡ ሲሰራ ፡ አያለሁ አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x) ውድቀቱን ፡ ለሚሹ ፡ ለሚመትቱበት ፡ በረከቱን ፡ ይዘው ፡ ሞት ፡ ለሚመኙለት ፡ ከሰማይ ፡ የሆነ ፡ ትንቢትን ፡ ይዣለሁ ፡ ለፃድቁ ፡ መልካም ፡ ይሆናል ፡ እላለሁ ፡ አንበጣ ፡ አይደለሁም ፡ ትንሽ ፡ ምናምንቴ ፈቃድን ፡ አልሰጠውም ፡ እንዲስቅ ፡ ጠላቴ በዘመኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ መልካሙን ፡ እናገራለሁ የኢየሱስ ፡ ወንጌል ፡ በህይወቴ ፡ ላይ ፡ ሲሰራ ፡ አያለሁ አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x) ለቅዱሳን ፡ ሁሉ ፡ ክፉ ፡ የመደባችሁ ሥም ፡ እየጠራችሁ ፡ እርገሙ ፡ ብሏቸው የተናገሩት ፡ ቃል ፡ ይሁን ፡ ለራሳቸው ያጠመዱት ፡ ወጥመድ ፡ ዞሮ ፡ ይያዛቸው አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.