Loading
የአምላኩን ፡ ምሥጋና ፡ ካፉ ፡ እወስዳለሁ በማመስገን ፡ ፈንታ ፡ ማጉረምረም ፡ እሞላለሁ ያለው ፡ ከሳሼ ፡ ሳይሆንለት ፡ ቀርቶ መላው ፡ ማንነቴ ፡ በደስታ ፡ ተሞልቶ ባሰብኝ ፡ ምን ፡ ትሆን ፡ ጠላቴ ባሰብኝ ፡ ይመስገን ፡ አምላኬ (፪x) ሳላይ ፡ የሚያይልኝ ፡ ሳልሰማ ፡ ሚሰማ ብጠራው ፡ ሚያደምጠኝ ፡ አምላክ ፡ አለኝና አለቴ ፡ ውስጥ ፡ ሆኜ ፡ ወደ ፡ ውጭ ፡ እያየሁ በሚፈልገኝ ፡ ላይ ፡ እስቅበታለሁ አዝ፦ አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ የማያልፈው ፡ ክፉ ፡ አጥቂ አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ (፪x) እልፍ ፡ ከሆኑት ፡ የጠላቴ ፡ እርግማኖች መልካም ፡ ካልሆኑት ፡ አሰናካይ ፡ ንግግሮች አንዲቱ ፡ ያምላኬ ፡ ምርቃት ፡ ከሱ ፡ እርግማን ፡ ትልቃለች እስከ ፡ ሺህ ፡ ትውልድ ፡ በበረከት ፡ ታኖራለች ይቀመጥ ፡ እንጂ ፡ ጠላቴ ፡ ሸንጎ በመንገዴ ፡ ላይ ፡ ወጥመድ ፡ አድርጎ ከራስ ፡ ፀጉሬ ፡ እስከ ፡ እግር ፡ ጥፍሬ አለኝ ፡ ዋስትና ፡ አልሰጋም ፡ እኔ አዝ፦ አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ የማያልፈው ፡ ክፉ ፡ አጥቂ አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.