Loading
ማን ፡ ጠገበ (ዬ) ፡ ማን ፡ ረካ ቃላት ፡ ቢደረደር ፡ በዝማሬ ፡ ተርታ እኔ ፡ በበኩሌ ፡ አልረካሁም አንተን ፡ የሚገልጥ ፡ ቃል ፡ አላገኘሁም እንዲያውም ፡ ለክብርህ ፡ ባሉኝ ፡ ቃላቶቼ ላደናንቅህ ፡ እንጂ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቼ (፪x) እንካ ፡ ጌታ ፡ ጣፋጭ ፡ ምሥጋናዬን ስለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ልግለጽ ፡ በዜማዬ (፪x) ቃልህን ፡ ልከኸው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ሰራ ከፊቴ ፡ ተነሳ ፡ የገዘፈው ፡ ያ ፡ ተራራ ታዲያ ፡ ለማመስገን ፡ ማን ፡ ከልክሎኝ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ከልካይ ፡ የለብኝም ፡ ተፈትቼ ፡ አመልካለሁ (፪x) ሌላ (፬x) ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ሌላ (፪x) የሚጤሰውን ፡ ጧፍ ፡ ሳታጠፋ ፡ ቅጥቅጡን ፡ ሸምበቆ ፡ ሳትሰብረው (፪x) ድምጽን ፡ ሳታሰማ ፡ ትመጣለህ ፡ ፍጥረትን ፡ መገረም ፡ ትሞላለህ (፪x) ልግባ ፡ ወደአንተ ፡ በአምልኮ በዐይኔ ፡ አሳይቶኛል ፡ ክንድህ ፡ ድንቅ ፡ ሰርቶ ተቀበለኝ ፡ ምሥጋናዬን ውዴ ፡ ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ይህን ፡ ስጦታዬን የአባቶች ፡ አምላክ ፡ ዘምርልሃለሁ አፌን ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ልቤን ፡ እሰጥሃለሁ (፪x) የሚጤሰውን ፡ ጧፍ ፡ ሳታጠፋ ፣ ቅጥቅጡን ፡ ሸምበቆ ፡ ሳትሰብረው (፪x) ድምጽን ፡ ሳታሰማ ፡ ትመጣለህ ፣ ፍጥረትን ፡ መገረም ፡ ትሞላለህ (፪x) ማን ፡ ጠገበ (ዬ) ፡ ማን ፡ ረካ ቃላት ፡ ቢደረደር ፡ በዝማሬ ፡ ተርታ እኔ ፡ በበኩሌ ፡ አልረካሁም አንተን ፡ የሚገልጥ ፡ ቃል ፡ አላገኘሁም እንዲያውም ፡ ለክብርህ ፡ ባሉኝ ፡ ቃላቶቼ ላደናንቅህ ፡ እንጂ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቼ (፪x) ሌላ (፬x) ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ሌላ (፫x) ሌላ (፪x) ፡ ሌላ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.