Loading
በቀንና ፡ በሌሊት ፡ አንተን ፡ እፈልጋለሁ ልቤም ፡ አንተን ፡ አለ ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ኢየሱስ ፡ እልሃለሁ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ እፎይ ፡ ምልብህ ፡ ውስጤ ፡ ያለውን ፡ ሁሉ ፡ ተንፍሼ በፊትህ ፡ ደስታ ፡ ሰላሜን ፡ ከልብስ ፡ ይልቅ ፡ ለብሼ ልቤ ፡ ከናፍቆት ፡ አንተን ፡ ከማለት ፡ አይቆጠብም ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆን ፡ ሚናፈቅ ፡ እንጂ ፡ አይጠገብም (፪x) አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ኢየሱስ ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ጣዕም ፡ ኢየሱስ (፪x) ከገሃነም ፡ ጥርስ ፡ በአንተ ፡ መዳኔ ፡ በዝቶ ፡ ሳያንስ በተከበበም ፡ መሃል ፡ ከተማ ፡ ሰላም ፡ ስትሆን እረፍቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ቅጥሬ ፡ እንዳይናድ ፡ በዓለም ፡ ሁካታ አብዝቼ ፡ እላለሁ ፡ አብረኸኝ ፡ ሆነህ ፡ ናፈቅከኝ ፡ ጌታ (፪x) ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ኢየሱስ ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ጣዕም ፡ ኢየሱስ (፪x) መሄድ ፡ መሄድ ፡ መሄድ ፡ ወዳንተ ፡ መገኛ ለነፍሴ ፡ ነውና ፡ ርሃቧ ቀና ፡ አልልም ፡ ሌሊት ፡ አልልም ፡ አብዝቼ ፡ እፈልግሃለሁ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ የመኖሬ ፡ አላማ ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ያለው ኦ ፡ አንተን ፡ ጌታ ፡ እፈልግሃለሁ (፪x) አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.