Loading
እዚህ ፡ እደርሳለሁ ፡ ብዬ ፡ አስቤ ፡ አላውቅም ከቶ ፡ በእኔ ፡ ጉልበት ፡ የሚቻል ፡ አይደለም ፡ የሚሆን ፡ አይደለም እርሱ ፡ በፈቃዱ ፡ ይህን ፡ ካደረገው ከመገረም ፡ ውጪ ፡ ሰዎች ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x) አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል አይደንቃችሁም ፡ ወይ ፡ ወገኖች ፡ በሙሉ ጌታ ፡ ያደረገው ፡ ለእኔ ፡ ለምስኪኑ እርሱ ፡ በኔ ፡ ሊከብር ፡ መስዋዕቴን ፡ ወዶታል በደረቁ ፡ አጥንቴ ፡ ዝማሬን ፡ ጨምሯል አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል ያዩኝ ፡ ይደነቁ ፡ እዚህ ፡ በመድረሴ በእርሱ ፡ ሆኖልኛል ፡ አይደለም ፡ በራሴ የማላገኘውን ፡ ዘመኔን ፡ ብሰራ ጌታ ፡ አደረሰኝ ፡ እስከ ፡ ጺዮን ፡ ተራራ ፡ ይገርማል አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል ከዘመን ፡ ዘመናት ፡ ወደዚህ ፡ አሻግሮ ቀድሞ ፡ እሱ ፡ ያየውን ፡ በልጁ ፡ ሰውሮ ዛሬ ፡ ተገለጠ ፡ ፍፃሜው ፡ አማረ ስንቱን ፡ ጉድ ፡ አሰኘ ፡ ስንቱ ፡ ተገረመ ፡ ይገርማል አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል የሚያየኝ ፡ ያክብርህ ፡ ይደነቅብህ በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ስትሰራ ፡ ያየህ ይናገር ፡ ክብርህን ፡ ምሥጋና ፡ ይጨምር ያው ፡ ነህ ፡ ለዘላለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ይገርማል አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል አደንቅሃለሁ ፡ አደንቅሃለሁ ያለኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ከተቀበልከው ፡ አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ ፡ አመልክሃለሁ ያለኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ከተቀበልከው ፡ አመልክሃለሁ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ቋንቋዬ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ከተቀበልከው ፡ እወድሃለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.