Loading
(ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው) ፡ ውርደቴን ፡ በክብር ፡ የለወጠልኝ (ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው) ፡ ሸክሜን ፡ ከላዬ ፡ ላይ ፡ ያራገፈልኝ (ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው) ፡ ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና ፡ ያረማመደኝ (ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው) ፡ በጌታዬ ፡ አደደል ፡ ዎይ ፡ የሆነልኝ (፪x) አዝ፦ መላ ፡ አለዉ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለው መላ ፡ አለዉ ፡ ጌትዬ ፡ መላ ፡ አለው አለው ፡ መላ ፡ ጌትዬ ፡ አለው ፡ መላ አለው ፡ መላ ፡ ውድዬ ፡ አለው ፡ መላ መላ ፡ አለዉ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ ጌትዬ ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ አባትሽ ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ የአንተ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለዉ በብዙ ፡ ክብር ፡ በብዙ ፡ ሞገስ ፡ ህዝቡን ፡ የረዳ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር እርሱ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ ተሟገተና ፡ እፎይ ፡ አስባለን ፡ መላ ፡ ሰጠና በብዙ ፡ ጭንቀት ፡ ውጣ ፡ ውረድ ፡ ደርሶ ፡ የሚያድነን ፡ ጌታ ፡ አባት እርሱ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ ተሟገተና ፡ እፎይ ፡ አስባለን ፡ መላ ፡ ሰጠና (እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ) ፡ መላ ፡ መድሃኒት (ከወዴት ፡ ይገኛል) ፡ ኧረ/እኮ ፡ ከወዴት (ሙሉው ፡ እርሱ ፡ ካለ) ፡ ለጠፋ ፡ ነገር (በቅዱሳን ፡ መሃል) ፡ ኦ ፡ ሥሙ ፡ ይክበር (፪x) አዝ፦ መላ ፡ አለው ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለው መላ ፡ አለው ፡ ጌትዬ ፡ መላ ፡ አለው አለው ፡ መላ ፡ ጌትዬ ፡ አለው ፡ መላ አለው ፡ መላ ፡ ውድዬ ፡ አለው ፡ መላ መላ ፡ አለዉ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ ጌትዬ ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ አባትሽ ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ የአንተ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለዉ ሞተ ፡ ተብሎ ፡ መቼ ፡ ተረሳ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ነሳ ትንሳኤ ፡ ሆነን ፡ ዳግም ፡ ለእኛ ቅኔን ፡ ተቀኘን ፡ ሆነን ፡ ተረኛ (፪x) (እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ) ፡ መላ/ያለ ፡ መድሃኒት (ከወዴት ፡ ይገኛል) ፡ ኧረ ፡ ከወዴት (ሙሉው ፡ እርሱ ፡ ካለ) ፡ ለጠፋ ፡ ነገር (በቅዱሳን ፡ መሃል) ፡ ኦ ፡ ሥሙ ፡ ይክበር (፪x) አዝ፦ መላ ፡ አለው ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለው መላ ፡ አለው ፡ ጌትዬ ፡ መላ ፡ አለው አለው ፡ መላ ፡ ጌትዬ ፡ አለው ፡ መላ አለው ፡ መላ ፡ ውድዬ ፡ አለው ፡ መላ መላ ፡ አለዉ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ ጌትዬ ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ አባትሽ ፡ መላ ፡ አለዉ መላ ፡ አለዉ ፡ የአንተ ፡ አባት ፡ መላ ፡ አለዉ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.