Loading
ልቤን ፡ ጣልኩት ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አሁንማ እኔስ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይጥለኝ ፡ የማይከዳ (፪x) በቁጥር ፡ ተቆጥሮ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ አይባልም አንተ ፡ ለኔ ፡ ያረግከው ፡ ሚዛን ፡ አይለካውም (፪x) አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ ብዬ ፡ ሙሉ ፡ አፌ ፡ ቢያወራ እኔስ ፡ ኮራሁብህ ፡ አምላክ ፡ የለኝ ፡ ሌላ (፪x ) አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ ብዬ ፡ (አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ ብዬ) ሙሉ ፡ አፌ ፡ ቢያወራ ፡ (ቢያወራ ፡ ቢያወራ) እኔስ ፡ ኮራሁብህ ፡ (ኮራሁ) ፡ አምላክ ፡ የለኝ ፡ ሌላ አዝ፦ ልቤን ፡ ጣልኩት ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አሁንማ እኔስ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይጥለኝ ፡ የማይከዳ (፪x) ተደላድያለሁ ፡ በርሱ ፡ ተወድጄ ዝማሬ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የሞላው ፡ በአፌ (፪x) ከእንግዲህ ፡ ወዲያ ፡ ልቤ ፡ አይገባም ፡ ስጋት ለሰው ፡ የሚያዝነው ፡ ሆኖልኛል ፡ አባት (፪x) ከእንግዲህ ፡ ወዲያ ፡ (ከእንግዲህ ፡ ወዲያ) ልቤ ፡ አይገባም ፡ ስጋት (አይገባም ፡ አይገባም) ለሰው ፡ የሚያዝነው ፡ (ኦ) ፡ ሆኖልኛል ፡ አባት (፪x) አዝ፦ ልቤን ፡ ጣልኩት ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አሁንማ እኔስ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይጥለኝ ፡ የማይከዳ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.