Loading
መነሻ ፡ ስፍራዬን ፡ አስታውሰዋለሁ ከየት ፡ እንዳነሳኸኝ ፡ መች ፡ እዘነጋዋለሁ ፀጋህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ማየቴ እጅህ ፡ ደግፎኝ ፡ ነው ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ ያማረው ፡ ሕይወቴ (፪x) ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ የሰመረው ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ ትርጉም ፡ ያገኘሁት ፡ ለመኖሬ ስለረዳኸኝ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ መዘመሬ ከየት ፡ እንደመጣሁ ፡ አስታውሰዋለሁ እራሴን ፡ አውቃለሁ የድሮው ፡ አድራሻዬን ፡ መች ፡ እረሳዋለሁ ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ ግን ፡ እንዲህ ፡ መቆሜ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው ኦ ፡ ከየት ፡ እንደመጣሁ ፡ እራሴን ፡ አውቃለሁ ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ ግን ፡ እንዲህ ፡ መቆሜ ፡ ከአንተ ፡ ይተነሳ ፡ ነው ከየት ፡ እንደመጣሁ ፡ አስታውሰዋለሁ እራሴን ፡ አውቃለሁ የድሮው ፡ አድራሻዬን ፡ መች ፡ እረሳዋለሁ ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ ግን ፡ እንዲህ ፡ መቆሜ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x) ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.