Loading
የጠላትህን ፡ ክስ ፡ ሊደመስስልህ ከዓብ ፡ ዘንድ ፡ የቆመ ፡ ጠበቃ ፡ አለልህ የኃጢአትህን ፡ ሸክም ፡ ተናዘህ ፡ እረፈው በደሙ ፡ ያጥበዋል ፡ ለኢየሱስ ፡ ንገረው አዝ፦ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ወንድሜ ፡ ከሳሽህ ፡ ተጥሏል የኃጢአትህ ፡ ዋጋ ፡ በጌታ ፡ ተከፍሏል ምህረቱን ፡ ተቀበል ፡ ኃዘንህን ፡ እርሳው ከንስሐ ፡ ወዲያ ፡ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሙላው በእድፋሙ ፡ ልብስህ ፡ ሰውነትህ ፡ ተከድኖ በአፍረት ፡ ተውጠህ ፡ በደልህ ፡ ተጋኖ ምንም ፡ ነገር ፡ ቢሆን ፡ "ከቶ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም" ብለህ ፡ ተሟገተው ፡ "ከፀጋው ፡ አልሸሽም" አዝ፦ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ወንድሜ ፡ ከሳሽህ ፡ ተጥሏል የኃጢአትህ ፡ ዋጋ ፡ በጌታ ፡ ተከፍሏል ምህረቱን ፡ ተቀበል ፡ ኃዘንህን ፡ እርሳው ከንስሐ ፡ ወዲያ ፡ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሙላው ጠላትህን ፡ ጥሎ ፡ እስራትህን ፡ ቆርጦ ክስህን ፡ ደምስሶ ፡ ፍርድህን ፡ ለውጦ ያ ፡ የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ምህረትን ፡ አውጇል ልብስህም ፡ እንዲቀየር ፡ ትዕዛዝን ፡ አውጥቷል አዝ፦ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ወንድሜ ፡ ከሳሽህ ፡ ተጥሏል የሃጥያትህ ፡ ዋጋ ፡ በጌታ ፡ ተከፍሏል ምህረትን ፡ ተቀበል ፡ ሃዘንህን ፡ እርሳ ከንስሃ ፡ ወዲያ ፡ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሙላው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.