Loading
የልቤን ፡ ስፈጽም ፡ አምላኬን ፡ ሳልፈራ ለኋለኛው ፡ ዘመን ፡ ሳከማች ፡ መከራ ኃጢአትን ፡ ስዘራ ፡ የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፀጋህ ፡ አሳመረው ፡ ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x) አዝ፦ እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳስተውል ፡ አርገኝ በቀረልኝ ፡ ዘመኔ ፡ ፈቃድህን ፡ እንዳደርግ ፡አስተምረኝ (፪x) ፈቃድህን ፡ አውቆ ፡ መታዘዙ ፡ ጠቅሞኝ ከኃጢአትም ፡ መራቅ ፡ ማስተዋል ፡ ሆኖልኝ መልካም ፡ ሥርዓትህን ፡ ተምሬ ፡ ተምሬ በእንግድነት ፡ ሐገር ፡ እዘምራለሁ ፡ ዛሬ አዝ፦ እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳስተውል ፡ አርገኝ በቀረልኝ ፡ ዘመኔ ፡ ፈቃድህን ፡ እንዳደርግ ፡አስተምረኝ (፪x) ፈቃድህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ የፈጸምከው ፡ በእኔ ለዛሬም ፡ ለነገም ፡ ባንተ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ዓይኔ በምሄድበትም ፡ መንገዴን ፡ አሳየኝ በቀረልኝ ፡ ዘመን ፡ ፈቃድህን ፡ አስታውቀኝ (፪x) አዝ፦ እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳስተውል ፡ አርገኝ በቀረልኝ ፡ ዘመኔ ፡ ፈቃድህን ፡ እንዳደርግ ፡አስተምረኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.