Loading
ያስፈልገኛል ያልኩትን ዞር ብዬ ተመልክቼ ካንተ ሚለዩኝን ነገሮች ዞር ብዬ ተመልክቼ ምንኛ ታልዬ ነበር ህይወትን የፈለኩት በሙታን መንደር በሌለህበት በሙታን መንደር ባልነገስክበት በሙታን መንደር በሌለህበት በሙታን መንደር ባልከበርክበት አሁንማ አሁንማ ውስጤ የለም ባዶ ቦታ አሁንማ አሁንማ ከብረህበት የኔ ጌታ አሁንማ አሁንማ ውስጤ የለም ባዶ ስፍራ አሁንማ አሁንማ ነግሰህበት የኔ ጌታ ጥያቄ የለኝም ምኞቴን አንድ ነው ዘመኔ እንድታልፍ ፊትህን እያየው ክብርህን እያየው ግርማህን እያየው ውበትህን እያየሁ/2 እግዚአብሔች ያለው ሁሉም አለው እግዚአብሔች ያለው ምንም አልቀረው ሰማያትን የዘረጋው ያከበረው ኧረ ምን ቀረው ኧረ ምን ቀረው እየሱስ ያለው ሁሉም አለው እየሱስ ያለው ምንም አልቀረው ሰማያትን የፈጠረው የወደደው ኧረ ምን ቀረው ኧረ ምን ቀረው አንተ በፈቀድከው መንገድ መሄድን ተስማምቼ አንተ በወደድከው መንገድ መሄድን ተስማምቼ ምንኛ ሰላም አገኘው ለነፍሴም እረፍት ከክብር ወደ ክብር አሻግረኸኝ/2 ክግርማ ወድ ግርማ አሻግረኸኝ/2 አሁንማ አሁንማ ለኔ የለም ሌላ ምርጫ አሁንማ አሁንማ መንገዴ ነህ አንተ ብቻ/2 ጥያቄ የለኝም ምኞቴን … እግዚአብሔች ያለው … ከተመስገን ሌላ ቃል አለ ውይ ላንተ ሚሆን ከተባረክ ሌላ ቃል አለ ውይ ላንተ ምሰጥህ ህይወቴን በፍቅርህ ሞልተኸዋልና ዙፋንህን ዛሬም ይክበበው ምስጋና ዘመኔን በቃልህ አስውበሃልና ዙፋንህን ዛሬም ይክበበው ምስጋና
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.