Loading
እኔም ፡ እንዲህ ፡ እንዲህ ፡ ወግ ፡ ደረሰኝ ከመቅበዝበዝ ፡ እርሱ ፡ በቃህ ፡ ሲለኝ ያ ፡ መራራ ፡ ሕይወቴ ፡ ጣፈጠ በኢየሱሴ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ አዝ፦ አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) እኔስ ፡ ገና ፡ ገና ፡ በልጅነት አይቻለሁ ፡ የጌታዬን ፡ ምህረት ሲርበኝም ፡ ከእጁ ፡ በልቻለሁ ያንን ፡ ሁሉ ፡ መች ፡ እዘነጋለሁ አዝ፦ አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) ማን ፡ ልበለው ፡ ምን ፡ ለበለው (፪x) በምን ፡ ቋንቋ ፡ በምን ፡ አንደበት ይነገራል ፡ የርሱ ፡ ደግነት (፪x) አይቼዋለሁ ፡ አይቼዋለሁ እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.