Loading
ማንም ፡ ያልፈታውን ፡ ማኅተም ፡ የፈታህ በትንሳዔው ፡ ጉልበት ፡ ሁሉንም ፡ የረታህ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሎ ገና ፡ ሁሉን ፡ ይገዛል ፡ ዳግም ፡ ተመልሶ (፪x) ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ በትንሳኤው ፡ ጉልበት ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ የረታ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው ለዚህ ፡ ሥም ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ማይገዛው ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካል አጋንንት ፡ ለሥሙ ፡ ይንቀጠቀጣል ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ኢሄ ፡ አምላካችን ገናናው ፡ ኢየሱስ ፡ መከታ ፡ ጋሻችን (፪x) መከታ ፡ ጋሻችን (፪x) ሰባቱን ፡ ከዋክብት ፡ በእጁ ፡ የያዘ በወርቅ ፡ መታጠቂያ ፡ ደረቱን ፡ የታጠቀ እንደ ፡ እሳት ፡ ነበልባል ፡ ዓይኖቹ ፡ ይህ ፡ ጌታ ፊቱም ፡ እንደፀሐይ ፡ ደምቆ ፡ የሚያበራ (፪x) ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ በትንሳኤው ፡ ጉልበት ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ የረታ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው ለዚህ ፡ ሥም ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ማይገዛው ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካል አጋንንት ፡ ለሥሙ ፡ ይንቀጠቀጣል ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ኢሄ ፡ አምላካችን ገናናው ፡ ኢየሱስ ፡ መከታ ፡ ጋሻችን (፪x) መከታ ፡ ጋሻችን (፪x) የመጀመሪያና ፡ መጨረሻ ፡ እርሱ ፡ ነው ዘለዓለም ፡ ያው ፡ ሆኖ ፡ በላይ ፡ የሚኖረው የመክፈት ፡ የመዝጋት ፡ ሥልጣን ፡ ሁሉ ፡ የእርሱ በሆታ ፡ በዕልልታ ፡ ኢየሱስን ፡ አንግሱ ፡ ስሙን ፡ አወድሱ ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ በትንሳኤው ፡ ጉልበት ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ የረታ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው ለዚህ ፡ ሥም ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ማይገዛው ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካል አጋንንት ፡ ለሥሙ ፡ ይንቀጠቀጣል ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ኢሄ ፡ አምላካችን ገናናው ፡ ኢየሱስ ፡ መከታ ፡ ጋሻችን (፪x) መከታ ፡ ጋሻችን (፪x) ውሃን ፡ አጣፈጠ ፡ ማዕበሉን ፡ አዘዘ በሙት ፡ በሲኦል ፡ ላይ ፡ ሥልጣኑን ፡ አሳየ ምን ፡ አለ ፡ በምድር ፡ ለእርሱ ፡ የተሳነው እኛም ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) አቤት (፬x) ፡ አቤት ፡ እንደኢየሱስ ማነው ፡ አቤት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬን እርሱን ፡ ማነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ውዴ ፡ ማነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ውዴ ፡ ማነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እርሱ ፡ መድሃኒት ፡ ነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው (ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.