Loading
አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል ጌታ ፡ ነዉ (፪x) ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ ኃያል ፡ ነዉ (፪x) ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ ፍቅሩ ፡ ተገልጧል ፡ ደግነቱ ተስፋ ፡ ለቆረጡ ፡ ማጽናናቱ አቤት ፡ ምሕረቱ (፬x) ምህረቱ ፡ አጽንቶ ፡ አቁሞኛል በኢየሱሴ ፡ ብርሃን ፡ ወጥቶልኛል ዘምራለሁ ፡ ንጉሤን ፡ አከብራለሁ የእርሱን ፡ ማዳን ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ አወራለሁ አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል ጌታ ፡ ነዉ (፪x) ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ ኃያል ፡ ነዉ (፪x) ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ አፌን ፡ በዝማሬ ፡ እከፍታለሁ የጌታዬን ፡ ክብር ፡ አወራለሁ ንጉሥ ፡ እለዋለሁ (፬x) እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ዘለዓለም ፡ ድንቅ ፡ ጌታ ይገባዋል ፡ ምሥጋና ፡ በዕልልታ ኦ! አክብሪው ፡ ነፍሴ ፡ ለእርሱ ፡ ተገዢ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ተስፋሽ አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል ጌታ ፡ ነዉ (፪x) ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ ኃያል ፡ ነዉ (፪x) ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ ዝማሬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ኦ! ምሥጋና ደግሜ ፡ ልባርከው ፡ ቸር ፡ ነውና ዛሬም ፡ እንደገና (፬x) ኦ! ጌታዬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አመልከዋለሁ ዘወትር ፡ ፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ አልሰለችም ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ብርታትና ፡ ኃይል ፡ ሆኖኛል አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል ጌታ ፡ ነዉ (፪x) ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ ኃያል ፡ ነዉ (፪x) ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.