Loading
ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ በእናቴ ፡ ማህጽን ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ እሮጥኩኝ ፡ እሮጥኩኝ ፡ ለብዙ ፡ ዘመን ፍቅርን ፡ የማገኘው ፡ በልፋት ፡ መስሎኝ ዝም ፡ አልከኝ ፡ እስክመጣ ፡ ድክሞኝ ፡ በቅቶኝ እጄን ፡ እስክሰጥህ ፡ መፍትሄ ፡ ጠፍቶኝ ታገስከኝ ፡ ልትለኝ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማነጻሽ ፡ ወደሃሳቤ ፡ ምመልስሽ እኔ ፡ ነኝ ፡ የመረጥኩሽ ፡ ወደ ፡ እራሴ ፡ የምስብሽ እኔ ፡ ነኝ ፡ የምለይሽ ፡ በፍቃዴ ፡ የማስኬድሽ ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ በእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ ሃሳቤን ፡ በሙሉ ፡ ከሩቅ ፡ ታውቀዋለህ የሥጋዬን ፡ ድክመት ፡ አዎ ፡ ታየዋለህ የለኝም ፡ ማቀርበው ፡ ከእኔ ፡ የሆነ በቅድስና ፡ ውስጥ ፡ ለመቆም ፡ የቻለ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ሚያስገባኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ሊቀ ፡ ካህን ፡ ለዘለዓለም የሚሽረው ፡ አንዳችም ፡ የለም X፪ በአንተ ፡ ፊት ፡ ሚማልድልኝ እንዳልጠፋ ፡ የሚዋጋልኝ ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ በእናቴ ፡ ማህጽን ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ በጨለማ ፡ ብሆን ፡ አንተ ፡ ብርሃኔ ፡ ነህ መንገዴንም ፡ ብስት ፡ ትመልሰኛለህ አልፈቀድክለትም ፡ ከሳሼ ፡ እንዲቀጥል ቀደህ ፡ እስክታስወግድ ፡ የጥፋቴን ፡ ዝርዝር ከፍለህ ፡ ዋጋዬ ፡ የሃጥያት ፡ እዳዬን አስታረከኝ ፡ ከአባቴ ፡ ጋራ በሰራኸው ፡ የመስቀል ፡ ስራ X፪ ወደኸኛል ፡ ገና ፡ ሳላውቅህ ይደንቀኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅርህ ኦ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ በእናቴ ፡ ማህጽን ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ይገርመኛል እኔስ ፡ ይደንቀኛል በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ X፪ ገና ፡ በሃጥያቴ ፡ ሳለሁ በፍቅር ፡ ዓይኖችህ ፡ ታየሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.