Loading
ማን ፡ ያመልጣል ፡ ከእግዚአብሔር ማን ፡ ይሸሸጋል ፡ ከጌታ ቢገለጥ ፡ ታሪካችን ጉድ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ ገበና በአደባባይ ፡ ጨዋ ፡ ያረገን በግል ፡ መክሮ ፡ ያሳፈረን ዳኝነቱ ፡ ያልተገባን እኔን ፡ ጨምሮ ፡ ቤቱ ፡ ይቁጠረን ነግ ፡ በእኔ ፡ ማለት ፡ ጥሩ በተያዙበት ፡ መያዝ ፡ ሳይያዙ ጌታን ፡ እንደው ፡ እርሱ ፡ ይምራል ይህንንም ፡ ይቅር ፡ ይላል (፪x) ምህረት ፡ የናቀ ፡ ዛሬም ፡ ይፈርዳል በተማረው ፡ ልክ ፡ ማን ፡ ሰው ፡ ይምራል (፪x) እንከን ፡ የለሽ ፡ ኑሮ ፡ የለኝም ታሪኬ ፡ ቢመረመር ሌላው ፡ ላይ ፡ ስፍረድ ፡ ቆሜ ወድቆ ፡ እስኪሰበር የእርሱን ፡ ገሃድ ፡ የእኔ ፡ በቤቴ ፍርድ ፡ ገምድሎ ፡ የማንነቴ ብዙ ፡ የተማረ ፡ ብዙ ፡ ይምራል ነበር ፡ ትምህርቱ ፡ ማን ፡ ግድ ፡ ይለዋል? አምላክ ፡ አድርጐለት ፡ ሃጥያቱን ፡ ታሪክ ሰው ፡ አልምር ፡ ብሎት ፡ ሆነ ፡ የዕድሜ ፡ ልክ አትፍረጅ ፡ አትፍረጅ ፡ ተይ ፡ ነፍሴ ይፈረድብሻል ፡ አንቺ ፡ ተይ ፡ ምላሴ እያየሽ ፡ እየኖርሽ ፡ የእርሱን ፡ ምህረት እንዴት ፡ ግድ ፡ አይልሸም ፡ የሰው ፡ ሕይወት የማያልፈው ፡ . (1) . ፡ የእራሱን ፡ ቁስለት አያቆም ፡ መፍረድ ፡ በሰውም ፡ ማንነት ለከፋ ፡ ቁስል ፡ እንጨት ፡ ይሰዳል ለታመመ ፡ ሰው ፡ ይህ ፡ መች ፡ ይረዳል ኧረ ፡ ያዛኝ ፡ ያለህ ፡ ይላል ፡ ጪኸቱ አላሳልፍ ፡ ቢለው ፡ የሰው ፡ አንደበቱ በሰው ፡ አፍ ፡ ተመቶ ፡ እያነከሰ ስንቱ ፡ ተሰብሮ ፡ ከማይሆን ፡ ዋለ ፡ አሃሃ ማን ፡ ያመልጣል ፡ ከእግዚአብሔር ማን ፡ ይሸሸጋል ፡ ከጌታ ቢገለጥ ፡ ታሪካችን ጉድ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ ገበና በአደባባይ ፡ ጨዋ ፡ ያረገን በግል ፡ መክሮ ፡ ያሳፈረን ዳኝነቱ ፡ ያልተገባን እኔን ፡ ጨምሮ ፡ ቤቱ ፡ ይቁጠረን ነግ ፡ በእኔ ፡ ማለት ፡ ጥሩ በተያዙበት ፡ መያዝ ፡ ሳይያዙ ጌታን ፡ እንደው ፡ እርሱ ፡ ይምራል ይህንንም ፡ ይቅር ፡ ይላል (፪x) ምህረት ፡ የናቀ ፡ ዛሬም ፡ ይፈርዳል በተማረው ፡ ልክ ፡ ማን ፡ ሰው ፡ ይምራል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.