Loading
አዝ፦ ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ተራራውን ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ያን ፡ ተራራ ተራራውን ፡ ስጠን ፡ ስጠኝ ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ እምነት ፡ አለኝ (፪x) ትወርሻለሽ ፡ ብሎ ፡ ቃል ፡ የገባልኝ አምላኬ ፡ የሰጠኝ ፡ ብዙ ፡ ርስት ፡ አለኝ አቅሜ ፡ ያለቀ ፡ የደከምኩ ፡ ብመስልም እምነቴ ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ አልነቃነቃም (፫x) አዝ፦ ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ተራራውን ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ያን ፡ ተራራ ተራራውን ፡ ስጠን ፡ ስጠኝ ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ እምነት ፡ አለኝ (፪x) ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ አይሎ ፡ ይታያል ኃይል ፡ ግን ፡ የለውም ፡ ጠላት ፡ ይወድቃል እንደ ፡ እንጀራ ፡ ነው ፡ ተቆርሶ ፡ ሚበላ ለጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ ጉልበቴም ፡ አይላላ (፫x) አዝ፦ ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ተራራውን ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ያን ፡ ተራራ ተራራውን ፡ ስጠን ፡ ስጠኝ ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ እምነት ፡ አለኝ (፪x) ሰላም ፡ በሌለበት ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ ትላለች ድምጿን ፡ ከፍ ፡ አድርጋ ፡ አብዝታ ፡ ዝታለኝ እባክህ ፡ አምላኬ ፡ ውጣ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ኤልዛቤልን ፡ ስጠኝ ፡ የህዝብህን ፡ . (1) . (፪x) ስጠኝ ፡ ኤልዛቤልን ፡ የህዝብህን ፡ . (1) . አዝ፦ ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ተራራውን ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ያን ፡ ተራራ ተራራውን ፡ ስጠን ፡ ስጠኝ ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ እምነት ፡ አለኝ (፪x) ባለራዕይ ፡ ደክሞ ፡ ጦረኛው ፡ ተማርኳል እምነቱ ፡ ዝሎበት ፡ ልቡ ፡ ሸፍቷል አስታጥቀኝ ፡ ለውጊያ ፡ አርገኝ ፡ ጦረኛ ለፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ለቤትህ ፡ ጉበኛ (፫x) አዝ፦ ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ተራራውን ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ያን ፡ ተራራ ተራራውን ፡ ስጠን ፡ ስጠኝ ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ እምነት ፡ አለኝ (፪x) ተዋግቶ ፡ ማሸነፍ ፡ ተለምምጃለሁ ስለ ፡ ተስፋ ፡ ቃልህ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ ስጠኝ ፡ ያን ፡ ተራራ ፡ አልታረሰም ፡ ገና ለመውጣት ፡ ለመውረስ ፡ ኃይል ፡ የአንተ ፡ ነውና (፪x) ለመውጣት ፡ ለመውረስ ፡ ጉልበቴ ፡ ነህና አዝ፦ ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ተራራውን ተራራውን ፡ ስጠኝ ፡ ያን ፡ ተራራ ተራራውን ፡ ስጠን ፡ ስጠኝ ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ እምነት ፡ አለኝ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.