Loading
ትልቅ ፡ የሆነውን ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድሜ መቼ ፡ አንገቴን ፡ ደፋሁ ፡ መች ፡ ሄድኩ ፡ አቀርቅሬ የተማመንኩበት ፡ ኩራቴ ፡ ሆኖኛል ትላንቴ ፡ ይመስክር ፡ ሰልፌን ፡ አሸንፏል ፤ ሰልፌን ፡ አሸንፏል (፪x) ከፍታውን ፡ ተመኝቶ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ፡ ያለ ላፍታ ፡ ማን ፡ ተመቸው ፡ ማን ፡ ተደላደለ ወርዷል ፡ ወደ ፡ ቦታው ፡ እርሱ ፡ ወዳዘዘለት ልክን ፡ ማወቅ ፡ እያለ ፡ ኋላ ፡ ከመዋረድ በዕውቀቱ ፡ ልቀት ፡ ማንስ ፡ ገለጠው እንኳንስ ፡ የእርሱን ፡ ጥግ ፡ ጫፉን ፡ ማን ፡ ነካው ሁሉም ፡ ከታች ፡ ሆኖ ፡ ይመለከተዋል የእጁ ፡ ስራ ፡ ሁሉ ፡ ሲያደንቀው ፡ ይኖራል ከቶ ፡ አልደፍርም ፡ አንደኛ ፡ ልለው ሁለተኛ ፡ ሆኖ ፡ ማን ፡ ተከተለው ሁሌ ፡ ብቻውን ፡ ሚመለክ ፡ ትልቅ ሚጨምር ፡ ክብር ፡ ከትላንቱ ፡ ይልቅ (፪x) ደጋግሞ ፡ ቢፎክር ፡ ቢጨምር ፡ ቀረርቶ ልኩን አግብቶታል ከሰማያት ፡ ወርዶ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ታዞ ፡ በመስቀል ፡ ላይ የአብን ፡ ጥም ፡ አርክቷል ፡ ሆኗል ፡ የአለም ፡ ሲሳይ ግድግዳው ፡ ፈረሰ ፡ በመሀከል ፡ ያለው ሰውን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ለይቶ ፡ ያቆየው ፍቅር ፡ መሀል ፡ ገብቶ ፡ ሁሉን : አንድ ፡ አረገ ጠላትም ፡ አፈረ ፡ ለሁሌ ፡ እጁን ፡ ሰጠ ከቶ ፡ አልደፍርም ፡ አንደኛ ፡ ልለው ሁለተኛ ፡ ሆኖ ፡ ማን ፡ ተከተለው ሁሌ ፡ ብቻውን ፡ ሚመለክ ፡ ትልቅ ሚጨምር ፡ ክብር ፡ ከትላንቱ ፡ ይልቅ (፪x) ትልቅ ፡ የሆነውን ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድሜ መቼ ፡ አንገቴን ፡ ደፋሁ ፡ መች ፡ ሄድኩ ፡ አቀርቅሬ የተማመንኩበት ፡ ኩራቴ ፡ ሆኖኛል ትላንቴ ፡ ይመስክር ፡ ሰልፌን ፡ አሸንፏል ፤ ሰልፌን ፡ አሸንፏል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.