Loading
ከሰማይ ፡ ሰማይ ፡ ወረደ እንደ ፡ በግ ፡ ለእኔ ፡ ታረደ ኢየሱስ ፡ ስለእኔ ፡ ታረደ መች ፡ አንዲህ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ነገሩ የኢየሱስ ፡ የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ (፪x) አዝ፦ አበሳዬን ፡ ወሰደው ፡ ከላዬ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ በሃፍረት ፡ መታያዬ ድፍረት ፡ ሆነኝ ፡ መግባት ፡ ወደ ፡ አባቱ አስታረቀኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ አማለደኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ (፪x) የህማም ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ ደቀቀ ኢየሱስ ፡ ስለእኔ ፡ ታመመ (፪x) መራራውን ፡ ጽዋዬን ፡ ጠጣ ሊያተርፈኝ ፡ ከሚመጣው ፡ ቁጣ ሊያድነኝ ፡ ከሚመጣው ፡ ቁጣ አዝ፦ አበሳዬን ፡ ወሰደው ፡ ከላዬ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ በሃፍረት ፡ መታያዬ ድፍረት ፡ ሆነኝ ፡ መግባት ፡ ወደ ፡ አባቱ አስታረቀኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ አማለደኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ (፪x) ይቅር ፡ በላቸው ፡ አባ ፡ ማራቸው ይህን ፡ ሁሉ ፡ ግፍ ፡ አትይባቸው ብለህ ፡ ማልደሃል ፡ በዛ ፡ ፈተናህ የሚያደርጉትን ፡ አያውቁምና ከሙታን ፡ በኩር ፡ ነህ ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳህ በአባትህ ፡ ቀኝ ፡ አለህ የይሁድ ፡ አምበሳ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.