Loading
ሀሳቤ ፡ የልቤ ፡ ባይሞላ ያቀድኩት ፡ ነገር ፡ ባይሰካ ላመስግን ፡ ልተው ፡ ማማረሬን ያልከው ፡ ይሁን ፡ ጌታ ያ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለእኔ አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x) ችግሬ ፡ ረሃቤ ፡ ቢፀናም ቁስሌ ፡ ባይደርቅ ፡ ፈውሴ ፡ ቢዘገይ ከፈቀድከው ፡ ይሁን ፡ ማለት አስተምረኝ ፡ ጌታዬ ፡ ትግስትን አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x) ጌታ ፡ ነህ ፡ ብትገል ፡ ብታድንም መከራከር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ኣይበጅም ክፉ ፡ አይደለህም ፡ ጨካኝ ለአላማህ : ነው ፡ ጌታ: የምትመራኝ አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x) አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሻለኛል የእራሴማ ፡ መቼ ፡ ያዋጣኛል ትርፉ ፡ መመረር ፡ መቁሰል ፡ ነው ለአንተ ፡ ሀሳብ :ጌታ ፡ መገዛት ፡ ጥሩ ፡ ነው አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x) በሥራህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ጻድቅ ፡ ነህ ተሳስተህስ ፡ መቼ ፡ ታውቃለህ ሀሳቤን ፡ በሀሳብህ ፡ ጠቅልለው ምኞቴንም ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ ቃልህ ፡ አርገው አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.