Loading
ላጫውትህ ፡ በዜማ ፡ ፊትህ ፡ ልዝለል ፡ ላሞጋግስህ ልንገር ፡ ማንነትክን ፡ ስምህን ፡ ልጥራ ፡ ላቆላምጥህ ልውጣ ፡ ከፊትህ ፡ ሆይታን ፡ ላብዛ ፡ ለምሥጋና በእኔ ፡ ዘንድ ፡ አንተ ፡ በዝቶ ፡ ያለህ ፡ ይህ ፡ ነውና (፪x) በምሥጋና ፡ እጅግ ፡ ከብረህ በክብርህም ፡ በጣም ፡ ልቀህ ተገኝትህ ፡ ሳለህ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይህ ፡ ያንስሀል ከዚህ ፡ በላይ ፡ ሊሆን ፡ ይገባል ምሥጋናህ ፡ በሕዝብህ ፡ መሃል (፫x) በበዛ ፡ ምሥጋና በበዛ ፡ ክብር ከፍ ፡ ባለ ፡ ምሥጋና ከፍ ፡ ባለ ፡ ክብር ክብር ፡ ተመስገን ፡ ለዘለዓለም (፬x) በእኔ ፡ ዘንድ ፡ በዝቶ ፡ አለህ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ምሥጋናህ ለነፍሴ ፡ ካረከው ፡ የመነጨ ፡ ከበጐ ፡ ስራህ የምሥጋና ፡ ነዶና ፡ ለስለቴ ፡ ምሥጋና ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፪x) ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፭x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.