Loading
አዝ፦ ያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ያው ፡ ነው ጥንትም ፡ የሚሰራ ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው አልተለወጠም ፡ ኃይሉ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ (፪x) (ሃሌሉያ) ባህሩን ፡ በተዓምር ፡ የከፈለ አንካሳውን ፡ ደግሞ ፡ ያዘለለ እውሩን ፡ በእጆቹ ፡ ዳሰሰና በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለው ፡ ፈወሰና (፪x) ጴጥሮስን ፡ በውሃ ፡ ላይ ፡ ያራመደ ማዕበል ፡ ወጀቡን ፡ ጸጥ ፡ ያረገ እንደሱ ፡ የሚሆን ፡ የትም ፡ የለም ይባረክ ፡ ይመስገን ፡ ለዘላለም (፪x) አዝ፦ ያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ያው ፡ ነው ጥንትም ፡ የሚሰራ ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው አልተለወጠም ፡ ኃይሉ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x) (ሃሌሉያ) ምንም ፡ በሌለበት ፡ ምድረ ፡ በዳ ሕዝቡን ፡ የሚመግብ ፡ የሚረዳ በጠሩትም ፡ ጊዜ ፡ ከተፍ ፡ የሚል የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያስተማምን በጠሩትም ፡ ጊዜ ፡ ከተፍ ፡ የሚል የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያስተማምን (፪x) ዛሬም ፡ ለኔ (ዛሬም ፡ ለኔ) ፡ በዘመኔ (በዘመኔ) ድንቅ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ (፪x) አዝ፦ ያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው ያው ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ያው ፡ ነው ጥንትም ፡ የሚሰራ ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው አልተለወጠም ፡ ኃይሉ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x) (ሃሌሉያ) እግዚአብሔርም ፡ እንዲህ ፡ ይላል ጥራኝ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ እሰማሃለሁ የማታውቀውን ፡ ታላቅና ፡ ኃይለኛ ፡ ነገር ፡ አሳይሃለሁ በቃሌ ፡ እኔ ፡ እተጋለሁ ፡ ድምጽህን ፡ ፈጥኜ ፡ እሰማለሁ ከቃሌ ፡ ጋራ ፡ እሆናለሁ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ እመን ፡ እሰራለሁ (፪x) ዛሬም ፡ ለኔ (ዛሬም ፡ ለኔ) ፡ በዘመኔ (በዘመኔ) ድንቅ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱሱ ፡ ጌታዬ ፡ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.