Loading
ህልምን ፡ ያሳየኸው ፡ ዮሴፍ ፡ ተጥሎ ፍርድ ፡ ተጣሞበት ፡ በእስር ፡ ቤት ፡ ተረስቶ አንተን ፡ የመጠበቅ ፡ ቢረዝምበት ፡ ጊዜው ጠጅ ፡ አሳላፊው ፡ አታስበኝ ፡ አለው ቀኑ ፡ ሲደርስ ፡ ግን ፡ በአንተ ፡ ተጐብኝቶ በችኮላ ፡ ወጥቶ ፡ ጸሎቱ ፡ ተሰምቶ ተለመነኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ተለመነኝ ልመናዬ ፡ ወደ ፡ ጆሮህ ፡ ይድረስልኝ ተለመነኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ተለመነኝ ጸሎቴ ፡ ወደ ፡ ማደርያህ ፡ ይድረስልኝ(፪) አቤቱ ፡ ልቤ ፡ ጨከነ(፬) እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ ኃይሌ ፡ ነው ፡ እያለ ሰው ፡ ምን ፡ ያደርገኛል ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አለ ልቤ ፡ ጨከነ አቤቱ ፡ ልቤ ፡ ጽኑ ፡ ነው(፬) በአምላኬ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይሌን ፡ አድሳለሁ ሰው ፡ ምን ፡ ያደርገኛል ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ልቤ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፊትህን ፡ የሚሹ ፡ በእኔ ፡ አይነወሩ ተስፋ ፡ የሚያደርጉህ ፡ አይተውኝ ፡ አይፈሩ በምሕረትህ ፡ ፊትህ ፡ አርግልኝ ፡ ጌታዬ ጉብኝትህ ፡ ይፍጠን ፡ በቤትህ ፡ በአገሬ ፍጠንልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ፍጠንልኝ እንደምሕረትህ ፡ ብዛት ፡ ፍረድልኝ ፍጠንልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ፍጠንልኝ እንደኃጢአቴ ፡ ከቶ ፡ አታርግብኝ (፪x) አበቱ ፡ ልቤ ፡ ጨከነ(፬) እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ ኃይለ ፡ ነው ፡ እያለ ሰው ፡ ምን ፡ ያደርገኛል ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አለ ልበ ፡ ጨከነ አበቱ ፡ ልበ ፡ ጽኑ ፡ ነው(፬) በአምላከ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይለን ፡ አድሳለሁ ሰው ፡ ምን ፡ ያደርገኛል ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ልበ ፡ ጽኑ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.