Loading
አዝ፦ ፍቅሩን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ምሕረቱን ፡ አይቼዋለሁ ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ያረገዉ ፡ መድኃኒቴ ኦ ፡ ኃያል ፡ ሥሙን ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x) ምሕረቱን ፡ አይቻለሁ (፪x) ፡ ላመልከው ፡ ፈቅጃለሁ ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ (፪x) ፡ ያረገው ፡ መድኃኒቴ ጉልበቴን ፡ አስገዛሁለት ፡ አምላኬን ፡ ሁሌ ፡ ላመልከው በፍቅሩ ፡ ስቦ ፡ ማርኮኛል ፡ ምሕረቱም ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው ስለዚህ ፡ ወደድኩት ፡ ለእርሱ ፡ ተገዛሁለት (፪x) አዝ፦ ፍቅሩን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ምሕረቱን ፡ አይቼዋለሁ ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ያረገዉ ፡ መድኃኒቴ ኦ ፡ ኃያል ፡ ሥሙን ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው ምሕረቱን ፡ አይቻለሁ (፪x) ፡ ላመልከው ፡ ፈቅጃለሁ ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ (፪x) ፡ ያረገው ፡ መድኃኒቴ ከእንግዲህ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል ፡ ሕይወቴን ፡ ሰጥቼዋለሁ ሌላ ፡ ማንም ፡ አይገዛኝም ፡ ለኢየሱስ ፡ ተለይቻለሁ በጣም ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ የአምላኬ/የጌታዬ ፡ ፍቅር ፡ ገዝቶኛል (፪x) አዝ፦ ፍቅሩን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ምሕረቱን ፡ አይቼዋለሁ ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ያረገዉ ፡ መድኃኒቴ ኦ ፡ ኃያል ፡ ሥሙን ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው ምሕረቱን ፡ አይቻለሁ (፪x) ፡ ላመልከው ፡ ፈቅጃለሁ ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ (፪x) ፡ ያረገው ፡ መድኃኒቴ እኔስ ፡ ፍቅሩን ፡ አይቻለሁ ፡ በድካም ፡ ቢሆን ፡ በብርታት ኢየሱስ ፡ ሁሌም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ወዳጄ ፡ ወረት ፡ የለበት ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ ምን ፡ ብለው ፡ ያረካኛል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.