Loading
፩) እኔኑ፡ ፍለጋ ፤ ዓመጸኛውን ፡ ሰው ተዋረድክ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ለሌለው እኔኑ ፡ ከውርደት ፡ ከማጥ ፡ አወጣኸኝ ተመስገን ፡ በልፋት ፡በጣር ፡ መጥተህ ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ (፪) እስኪ ፡ አስቡት ፡ ጌታን! አቤቱ! ማንስ ፡ ይወድህ ፡ ዘንድ? ሃሌሉያ! ማንም ፡ እንዲወድህ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ የለህም የሕማም ፡ ሰው ፡ ነበርክ ፡ ደዌ ፡ ያደቀቀህ በመገረፍህ ፡ ቁስል ፡ እኔ ፡ የተፈወስኩት በመስቀል ፡ በመሞትህ ፡ከሞት ፡ አመለጥኩኝ ፤ ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ ፡ ፡ (፪) እስኪ ፡ የተደረገልንን ፡ እናስባለን! የቀራንዮን ፡ ፍቅር ፡ እናስባለን! በመከራ ፡ ሰዓት! በመከራ ፡ ሰዓት ፡ በዚያ ፡ ጭንቀትህ ዓብ ፡ አባትህ ፡ እንኳ ፡ ዝም ፡ አለ ፡ ተወህ የሁላችን ፡ በቀል ፡ በላይህ ፡ ላይ ፡ ሆነ በመስቀል ፡ እንዳንተ ፡ የለም ፡ የታመነ ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው ፡ ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ (፪) ሃሌሉያ! ስለእኛ ፡ የታረድክ! ለዘላለም ፡ ተባረክ! የእኛ ፡ ጌታ! ልታዘዝህ ፡ ዛሬ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ ክብርህን ፡ ላያት ፡ ጣርህን ፡ አስቤ ዋጋ ፡ ከፍለህልኝ ፡ ሰው ፡ አድርገኸኛል ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ደምህ ፡ ፈሶልኛል ኤሎሄ ፡ ላማሰበቅታኒ ፡ እስክትል ፡ የተሰቃየኸው ስለእኔ ፡ ሞትህ ፡ ልታድነኝ ፡ በበዛው ፡ የመስቀል ፡ ጣርህ ስለእኔ ፡ ለከፈልከው ፡ ዋጋ መታሰቢያ ፡ ላድርግ ፡ እስኪ ፡ ዛሬ ለመክፈል ፡ ዋጋ ፡ ካሣ ፡ ባይኖረኝም ላክብርህ ፡ በፊትህ ፡ ዘምሬ (፪x) ሃሌሉያ!
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.