Loading
አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና ላይሞላልኝ ፡ ላይሳካልኝ ከእቅፍህ ፡ ምን ፡ አወጣኝ ለውድቀቴ ፡ ምክንያቱን ፡ ደርድሬ ይቆጨኛል ፡ ሳስበው ፡ ዛሬ አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና በሚመለስ ፡ ደስ ፡ ይልሃልና ፊትህ ፡ መጣሁ ፡ ይኸው ፡ እንደገና ክብር ፡ የለም ፡ ውርደት ፡ ነው ፡ ዓለም ፡ ያለው ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መኖር ፡ ሰላም ፡ ነው አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና ከህልውናህ ፡ ሚሻል ፡ ምን ፡ አለና መገኘትህ ፡ በቂ ፡ ነውና እህል ፡ ውኃ ፡ ሞልቶ ፡ ሳይጐለኝ ክብርህ ፡ ጌታ ፡ ውስጤን ፡ ራበኝ አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.