Loading
አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x) አባት ፡ እንደሌለው ፡ አልተዋችሁም ስፍራን ፡ ላዘጋጅ ፡ እንጂ ፡ እንድወስዳቹህ ልባቹን ፡ አይፍራ ፡ በእኔ ፡ እመኑ ቶሎ ፡ እመልሳለሁ ፡ ልወስዳቹህ አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x) እንኳን ፡ መኖሪያችን ፡ ቤታችን ሊፈርስ ፡ ተስፋ ፡ ቢያጣ ፡ ኑሯችን በእጅ ፡ ያልተሰራ ፡ ጌታ ፡ ያዘጋጃል ተስፋችን ፡ ላይኛይቱ ፡ ጽዮን ፡ ናት አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x) በዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሯችን ፡ ያበቃል ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሊወስደን ፡ ይመጣል ብርሃን ፡ በሞላባት ፡ ቅድስት ፡ ሃገር ጊዜው ፡ ደርሷል ፡ እንሂድ ፡ እንዘምር አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.